ገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ / Gente Tsige st.Gorge E/O/T church Dallas,TX

ገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ / Gente Tsige st.Gorge E/O/T church Dallas,TX

Comments

ከፍጥረት ድንግል ማርያምን የሚያክል ተአምር የሰራ ማን ነው???? (አምላክን ከመውለድ የሚበልጥ ተአምር ይች ምድር ምን አላት??? (ይህንን ተአምረ ማርያምን የምትንቁ ሰዎች እንድትመልሱት እፈልጋለሁኝ (ኤርምያስ ጌትዬ 2011.መጋቢት.27)
ከፍጥረት ድንግል ማርያምን የሚያክል ተአምር የሰራ ማን ነው???? (አምላክን ከመውለድ የሚበልጥ ተአምር ይች ምድር ምን አላት??? (ይህንን ተአምረ ማርያምን የምትንቁ ሰዎች እንድትመልሱት እፈልጋለሁኝ (ኤርምያስ ጌትዬ 2011.መጋቢት.27)
አሜን
አቤቱ፡አምላኬ።

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን:: የሊቀ ሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ዝርዎተ ዓፅሙ በዓለ ንግስ በገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢ/ኦ/ቤ/ክ
ጥር 18/2011 ወይም January 26, 2019 ዓ.ም
በታላቅ ድምቀት ስለምታከብር ሁላችሁም ተገኝታችሁ የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በልዑል እግዚአብሔር ስም ተጋብዛችኃል:: ሁላችንም share በማድረግ ለወጃጆቻችን እንዲሁም ለጏደኞቻችን እንዲዳረስ እንተባበር:: የልዑል እግዚአብሔር ሰላም ከሁላችንም ጋር ይሁን:: አሜን!!

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን::

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በአለ እርገት በሰልም አደረሰን ::

"ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር"

እመቤታችን ከእናትና ከአባቷ ዘንድ ሦስት ዓመት፣ በቤተ መቅደስ 12 ዓመት፣ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ 33 ዓመት ከሦስት ወር፣ ከዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ዘንድ 14 ዓመት ከዘጠኝ ወር ጠቅላላ ድምር 64 ዓመት ሲሆናት ጥር 21 ቀን አርፋለች፡፡
ነቢያት አስቀድመው ስለ እመቤታችን እረፍትና ትንሳኤ በምሥጢር ተናግረዋል፡፡
ነቢዩ ዳዊት በመዝሙሩ፡- መዝ 136፡8 “አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት” ብሎአል፡፡ ፈጣሪዬ ሆይ ምእመናንን ወደምታሳርፍበት ወደ መንግሥተ ሰማያት የመቅደስህን ታቦት ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ ሲል ነው፡፡ ይህም እመቤታችን እንደ ልጅዋ ትንሣኤ መነሣቷን የሚያመለክት ነው፡፡ ታቦት ያላትም ማደሪያው ስለሆነች ነው፡፡
ጠቢቡ ሰሎሞንም “ወዳጄ ሆይ ተነሺ ውበቴ ሆይ ነይ እነሆ ክረምት አለፈ ዝናቡም አልፎ ሄደ አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፡፡ የዜማም ጊዜ ደረሰ የቀረ… ቃል በምድራችን ተሰማ፡፡ በለሱ ጐመራ ወይኖችም አበቡ መዓዛቸውንም ሰጡ፡፡ ወዳጄ ሆይ ተነሺ ውበቴ ሆይ ነይ” ሲል ስለ እመቤታችን በምሳሌ ተናግሮአል፡፡ መኃ 2፡10-13
ወዳጁን ውበቱን ተነሺ ነይ እያለ የተጣራው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ተጠሪዋም እመቤታችን ናት፡፡ እነሆ ክረምት አለፈ ማለት በስደት በአይሁድ የዘወትር ጠላትነት በልጅዋ መከራና ስቅላት ስምዖን በቤተ መቅደስ እንደተናገረ ልቧ በሀዘን ሠይፍ የተከፈለበት በሀዘን ፍላጻ የተወጋበት የመከራ ክረምት /ወቅት/ አልፎ የክርስቶስ ሕማሙ ፣ ሞቱ፣ ቤዛነቱ ተፈጽሟል፡፡ ትንሣኤው በምድር ላይ ተገልጧል፣ ተሰብኳል ማለት ነው፡፡ በምድራችን አበባ ታይቷል ማለት የሐዋርያት ድምፅ በምድር ሁሉ ደርሷል ማለት ነው፡፡ ነቢዩ ዳዊት ‹ ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ › ብሎ ስለ ሐዋርያት የተናገረው በዓለም ያለውን መከራ ስደት ሲገልጽ ነው፡
‹የዜማም ጊዜ ደረሰ ያለው የመከራን ጊዜ ነው፡፡ ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ በደስታ ይጮሃሉ፣ ይዘምራሉም› ተብሏል፡፡ መዝ 14፡13 የመከር ጊዜ ደረሰ የተባለው መከር የፍሬ ጊዜ በመሆኑ ክርስትና አፍርቷል ማለት ነው፡፡ በለሱ ጐመራ ማለት ደግሞ በጐ ምግባረ ፍሬ ሳያፈሩ የነበሩ ሰዎች በጐ ምግባር መሥራት መጀመራቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ በመጨረሻም ወይኖች አብበዋል፣ መዓዛቸውንም ሰጥተዋል እንደተባለ በመላው ዓለም አብያተ ክርስቲያናት በሃይማኖት ማበብ መዓዛ ምግባራቸውን ማቅረብ ከጀመሩ በኋላ እመቤታችን አረፈች፡፡
የእግዚአብሔር መልአክ የእመቤታችን ሥጋ ከሐዋርያው ዮሐንስ ጋር ተድላ ደስታ ወደ አለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቁ፡፡ ጌታም የእመቤታችንን ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው፡፡ እነርሱም ትወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አሏት፡፡ ያን ጊዜም ከእፅ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን የማርያም ሥጋዋ ወጣ፡፡ ጌታችንም ዘላለማዊ ወደሆነ መንግሥተ ሰማያት መላእክት እና ሰማእታት እየሰገዱላት አሳረጓት፡፡ ንጉሥ ዳዊት “በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋ ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች” እንዳለ፡፡ መዝ 44፡9
ጌታችን ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሰ መቃብር ቆይቶ ሙስና መቃብር ሳያገኘው፣ መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በሥልጣኑ እሑድ በመንፈቀ ሌሊት እንደተነሣ ሁሉ እርሷም በተቀበረች በሦስተኛው ቀን ማኅደረ መለኮት ናትና ሙስና መቃብር ሳያገኛት መግነዝ ፍቱልኝ፣ መቃብር ክፈቱልኝ ሳትል የልጅዋ ሥልጣን ኃይል ሆኗት መነሣቷን ትንሣኤዋ “ከመ ትንሣኤ ወልዳ፤ እንደ ልጅዋ ትንሣኤ” ነው ተብሎ ሲከበርላት ይኖራል፡፡ የእመቤታችን የንጽህተ ንጹሃን የቅድስተ ቅዱሳን ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ረድኤት በረከት በሁላችንም ላይ ይደር እጥፍ ድርብም ይሁን:: የእመቤታችን አማላጅነቷ አይለየን አሜን፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አኃዱ አምላክ አሜን
„እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ:“ ሉቃስ 1፣19
በቅድሚያ ሰላመ እግዚአብሔር አይለያችሁ እያልን የሐምሌ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ሐምሌ 22.07.2018 ዓ.ም በደብራችን በድምቀት ይከበራል::
ስለሆነም በቦታው ተገኝታችሁ የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል በረከት ተካፋዮች እንድትሆኑ ተጋበዛችኋል::

ሰላመ እግዚአብሄር ከሁላችን ጋር ይሁን!!!

የአባታች የፃዲቁ የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ በአለ እረፍት ክብረ በአል በታላቅ ድምቀት በገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተከበረ:: የፃዲቁ የአባታችን ልመናቸውና ፀሎታች ረድኤትና በረከታቸው በሁላችንም ላይ ይደርብን ::አሜን!!

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።
እንኳን ለአባታችን ለፃዲቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አመታዊ ክብረ በአል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ። የዳላስ ቴክሳስ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአባታችን የፃዲቁ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የመጋቢት 5 በዓለ እረፍቱን በደማቅ ስለምታከብር ሁላችሁም በቦታው በነገኘት የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በልዑል እግዚአብሔር ስም ቅድስት ቤተክርስትያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

[02/15/18]   በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን !
አብይ ፆም
አብይ ፆም መባሉ ትልቅና ታላቅ ፆም መሆኑን ለማሳወቅ ነው። ይህ ፆም ታላቅ መባሉም ለ፶፭ ቀናት ያህል መፆሙ እና ከሌሎቹ አፅዋማት ጋር ሲነፃፀር በቁጥር መብለጡ ብቻ ሳይሆን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንቶስ መፆም ሳይገባው ለእኛ አርአያ እና ትልቅ ምሳሌ ለመሆን የፆመው ፆምም በመሆኑ ነው።
ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ መልእክት ላይ የተሰኘውን አምላካዊ ቃል (ሉቃ.፲፱፡፲)አስፍሮልን ስንመለከት አምላካችን ወድ ምድር መምጣቱ የሰውን ልጅ ከውድቀቱ ሊያነሣው መሆኑ ሳይነገር የታወቀ ሳይታለም የተፈታ ነው። ዲያብሎስም በበኩሉ ባለው የማጥመጃ መሳሪያና የማሰሪያ ሰንሰለት ተጠቅሞ የሰውን ልጅ ከአምላክ አለያይቶ፣ ከተድላው አርቆ፣ ከገነት አውጥቶ፣ የመንግሥተ ሰማያትን መንገድ አዘግቶ እና ዘላለማዊ ሕይወትን አሳጥቶ መኖርን ስለሚፈልገው በተቻለው ሁሉ ይህንን ግብሩን ሲያደላድል ይኖራል። መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕይወት እንድንደርስ ሳያሸልብ እንደሚጠብቀን ሁሉ ከሳሽ ዲያብሎስም ሳያሸልብ መውደቂያችንን ሲያመቻች ይኖራል።
በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፬፡፩-፲፬ አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ እጅ ከተጠመቀ በኋላ ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ በመሄድ ፵ ቀንና ፵ ሌሊት እንደ ጦመ በዚያም በዲያብሎስ እንደተፈተነና ዲያብሎስን ድል እንዳደረገው ተዘግቦ ይገኛል። በፆም ድል ማድረግን ጌታ ያስተማረን ከሳሽ ዲያብሎስ አዳምና ሔዋንን ባሳተበት ግብሩ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነውን ጌታ ሥጋ ለብሶ ቢያየው ከመጽሐፍ ጥቅስ እየጠቀሰና የእግዚአብሔርን ቃል እየተናገረ ሊያስተው ቢሞክርም አሳች ዕቅዱ መክኖ መቅረቱን ነው።
ዮሐንስ በአንደኛ መልዕክቱ ምዕራፍ ፫፡፰ ላይ እንዳለው ሁሉ በ፵ ቀንና በ፵ ሌሊት ፆም የዲያብሎስ ሥራ ሲፈራርስ ታየ። አዳምን በመብል ያሳተ የቀደመው እባብ ሰይጣን ዲያብሎስ ዳግም በመብል ፈትኖ ገነት እንደተዘጋች እንድትኖር ቢያልምም ኅልሙ እውን፣ ሙከራው አዎንታዊ፣ ጥረቱ ተግባራዊ ሳይሆን ቀርቷል። የዲያብሎስን ሥራ ሊያፈርስ የተገለጠው የእግዚአብሔር ልጅም በፆም ድል ማድረግን ለእኛ አስተምሮናል። እኛም በዚህ በአብይ ፆም የለመነውና የጠየቅነው ነገር ሁሉ ከኃጢአት በስተቀር እንዲከናወንልን ፆምን ገንዘባችን እናድርግ። በፆም የተጠቀሙ ቅዱሳን አባቶችና ቅዱሳን እናቶች እንዳሉን እናስተውል። በተለይ አሁን በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ በሚታየው አስቸጋሪ ፈተና እያንዳንዳችን ልባዊ ፆም በመፆም ልዑል እግዚአብሔር የፀሎታችንን ምላሽ እንዲሰጠን እንማፀን።
ከዚህ በታች ደግሞ ቤተ ክርስቲያናችን የስምንቱ አበይት ሳምንታትን ስያሜ ቀድማ እንዳዘጋችልን የታወቀ በመሆኑ እኛም ደግሞ የእነኝህን ሳምንታት ስያሜ በማገናዘብ፣ ምሥጢራቸውንም በመረዳት ፆማችንን እንድናስብ በቅደም ተከተል አስፍረናቸዋል። ዘወረደ

፪- ቅድስት

፫- ምኩራብ

፬- መጻጉዕ

፭- ደብረ ዘይት

፮- ገብርኄር

፯- ኒቆዲሞስ

፰- ሆሣዕና

አንደኛ ሰንበት(ሳምንት)፦ ዘወረደ ተብሎ ይታወቃል።

በዚህ ቀን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ ወደ ምድር መውረድ ይሰበካል ይዘመራል። ሰውም በታላቅ ፍርሃትና ወደ አምላክ መቅረብ እንዳለበት ይነገርበታል።ምስባኩም፦ መዝ.፪፡፲፩ ነው። ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ወተሐሰዩ ሎቱ በረዓድ
አፅንእዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዐፅ

ትርጉም :-ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ በርአድም ደስ ይበላችሁ
ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቆጣ.

የሊቀ ሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ዝርዎተ አፅሙ ክብረ በአል በታላቅ ድምቀት በገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተከበረ:: የሰማዕቱ ረድኤትና በረከት በሁላችንም ላይ ይደርብን ::

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን:: የሊቀ ሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቅጥቃጤ ዐፅሙ በዓለ ንግስ ቤተክርስቲያን በታላቅ ድምቀት ስለምታከብር ሁላችሁም ተገኝታችሁ የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በልዑል እግዚአብሔር ስም ተጋብዛችኃል:: ሁላችንም share በማድረግ ለወጃጆቻችን እንዲሁም ለጏደኞቻችን እንዲዳረስ እንተባበር:: የልዑል እግዚአብሔር ሰላም ከሁላችንም ጋር ይሁን:: አሜን!!

[09/27/17]   " ወይንሳዕ መስቀለ ሞቱ ወይትልወኒ - የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ"

ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቃል መነገሩ፣ በኅሊና መዘከሩ፣ በሰው ልብ መታሰቡ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት መዘገቡ ከፍ ይበልና፣ ጌታችንንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛ ልጆቹ ፈቃዱን እያደረግን እንድንኖርና እርሱም ከመልካም ምግባራችንና ከበጎ ትሩፋታችን ብቻ የተነሳ ፍጹማን እንደማንሆን ያውቃልና፣ ከማያልቅ ልግስናው ከማይጓደል ምሕረቱ ዘመናትን እየመጸወተን ደስ የሚሰኝበትን ለእኛ እያደረገ በቸርነቱ ያኖረናል:: ከእርሱና ከዓላማው ጋር ጸንተን እንድንኖርም እንዲህ ሲል በቅዱስ ወንጌል አዝዞናል:: “ዘይፈቅድ ይትልወኒ ይጽላዕ ነፍሶ ያጥብዕ ወይንሳዕ መስቀለ ሞቱ ወይትልወኒ (እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ) ወምንተ ይበቁዖ ለሰብእ ለእመ ኩሎ ዓለመ ረብሐ ወነፍሶ ኃጉለ (ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?)” (ማቴ. 16:24-26)።

ጥንቱንም ቢሆን እኛ የተፈጠርነው በሕይወት እንድንኖር ነው። ትንሳኤና ሕይወት ክርስቶስ ግን የተወለደው ስለኛ እንዲሞት ነው:: በዚህም ሁላችን ለእርሱ እንድንኖር እርሱ ስለ ሁላችን ሞተ “በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ። “(1ቆሮ፣ 5:15)። ይህ ግን መስቀል የገደለው ያይደለ ይልቁንም በመስቀሉ ሞትን ገደለበት እንጂ:: “በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።” (ፊል. 2:8) እንዲል::

ሊከተለኝ የሚወድ ነፍሱን ይጥላ አለ፣ ይህም ነፍሱንና ሥጋውን የሚለይ መከራ ለመቀበል ይጨክን ሲል ነው። ሰውስ ለክርስትና ፍኖቱ ለነፍሱ ሥምረት እያደረ የሥጋውን ፈቃድ እየገፋና እየጠላ ሊኖር ይገባዋል። ለዚህም ጌታችን ተከታዩን ሃሳብ እንዲህ ሲል አስፍሮታል “ወምንተ ይበቁዖ ለሰብእ ለእመ ኩሎ ዓለመ ረብሐ ወነፍሶ ኃጉለ፤ ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?” መከተሉም ቢሆን ሌጣውን ያይደለ የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይለናል::

መስቀል ምንድር ነው ?

መስቀል በቀደመው ዘመን ለኃጢአተኞች እግዚአብሔርን ለበደሉ መቅጫ የነበረ “በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና” (ዘዳ፣21:23)። ነገር ግን በአዲስ ኪዳን ለክርስቲያኖች ኃይል፣ ጽንዕ፣ ቤዛና መድኃኒተ ነፍስ ሆኖ የሚያገለግል አርማ ነው:: ወደዚህ ክብር እንዴት ሊሻገር እንደቻለ ሊያስረዱ የሚችሉ በመስቀሉ ከተፈጸሙ ድንቅ መንክራት እፁብ ተዓምራት መካከል ተከታዮቹን ሦስት ዓበይት ነጥቦች እንደእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ እንመለከታለን::

+ ጠላት የራቀበት ነው።

መስቀል የቀደመው እባብ የዲያቢሎስ ራስ የተቀጠቀጠበት እኛም ድል መንሳትን በግልጥ ያየንበት እጸ መድኃኒት ነው:: “በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው። እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል።አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ (በመስቀል) እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው።” (ቆላ፣ 2:14) እንዲል።

+ እኛ የቀረብንበት ነው።

ተመልከቱ ራሱን ወደኛ ያቀረበበት ነው አላልንም “አመ ተለአልኩ እምድር እስህብ ኩሎ ኃቤየ፤ እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ።” (ዮሐ፣12:32) እንዳለ እኛን ወደራሱ አቀረበበት፣ ምክንያቱም ሰው በድሎ ራቀው እንጂ እርሱ ከሰው የተለየበት ጊዜ አልነበረምና። “እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ የሩቅ አምላክ አይደለሁም።” (ኤር፣23:23) እንዳለን። ይበልጡንም ለተዛምዶ ረቂቅ ቅርበቱ ያይደለ ሥጋችንን ነስቶ አማኑኤል ተሰኝቷል። “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ።” ይህም በኩነት ታዲያ ዓላማው ወደእኛ መቅረብ ብቻ ቢሆን ይህ ልደቱ በበቃው ነበር። መስቀሉ ግን ወደኛ መምጣቱን ባንቀበል ወደራሱ ሊወስደን ወደ ሰማይ ቤታችን ሊስበን በቀራንዮ ተተከለ። ለዚህም ሊቁ ማር ኤፍሬም “አቅረበነ ኃቤሁ ዘዚአነ ሞተ ነሳ ወእንቲአሁ ሕይወተ ወኃበነ- ወደራሱ አቀረበን የእኛን ሞት ወስዶ የእርሱን ሕይወት ለእኛ ሰጠን” ሲል መነሻችንን ያስረዋል።

+ የጥል ግድግዳ የፈረሰበት

ሰው የሞትን እጽ ቆርጦ ቢበላ አምላኩን በደለ። በዚህም የጸብ ግድግዳ ተተከለ። ሰው ከአምላኩ ተለየ ልዑለ ቃል ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ “ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች፥ እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።” (ኢሳ፣59:2) ሲል እንደገለጸው፣ ታዲያ ከህገ ልቡና ወደ ህገ ኦሪት መሻገሩ ፍጻሜ ያለው ድኅነት ሊያመጣ ባለመቻሉ የሚበልጥና የሚሻል አዲስ ኪዳን የሚሰጥበት አዲስ መስዋዕት የሚሰዋበት አዲስ ድንኳን አስፈለገ (ዕብ፣ 9:11)። ለዚህም የአዲስ ኪዳን ሥርዓት ክቡር ደሙ የፈሰሰበት የሕይወት ህብስት ቅዱስ ሥጋው የተቆረሰበት ዐረፍተ ማእከል የተናደበት እጸ መድኃኒት ቅዱስ መስቀሉ ተሰጠን። “እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው።” (ኤፌ፣ 2:15)።

እንግዲህ በጠቅላላው መስቀል የምንለው፣ በቁሙ ከቤተክርስቲያን ጉልላት እስከ ምዕመናን ንቅሳት የሚታይ የድል ምልክት፣ በሰሌዳ ተስሎ በጣት ተመሳቅሎ የሚገኝ የድኅነት አርማ፣ ካህናት በእጃቸው ይዘው የሚፈቱበት፣ ክርስቲያኖች በአንገታቸው አስረው ማንነታቸውን የሚመሰክሩበት መገለጫ ሲሆን. በሌላ አገባብ መከራ የተጋድሎ ፍኖት ማለት ነው።

እግዚአብሔር ወልድ ክርስቶስ ስለሁላችን መዳን መከራን ተቀብሎልናል። እናስተውል፣ እያንዳንዳችን በመዳን ኑሮ ሐሳባችን፣ እቅድ ምኞታችን በመከራው ልንካፈለው፣ በሞቱ ልንመስለው ፈለጋውን ልንከተለው ይገባናል።

“ስለዚህ ኢየሱስ ደግሞ በገዛ ደሙ ሕዝቡን እንዲቀድስ ከበር ውጭ መከራን ተቀበለ። “(ዕብ፣13:12) እንደተባለ፤ ከበር ውጪ አለ በቀራንዮ ኮረብታ የራስ ቅል በተባለ ጎልጎታ ሊቀድሰን ተሰቀለ። እኛ ክርስቶስ በደረሰበት መከራ ከድቅድቁ ጨለማ ድንቁርና ወደሚደነቀው ብርሃን እውቀት የተሻገርነው፣ ስለ አዳም በደል መከሰስን ጥለን ስለራሳችን ጽድቅ መከራን በመቀበል እንድንከተለው ነው:: ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ “የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና። “(1ኛ፣ጴጥ.2:21) ሲል እንዳስረዳን። በዚህም ኅሩይ ነዋይ ቅዱስ ጳውሎስ “እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ። “(ፊል.3:10-11)። ሲል ምኞቱን አስረዳን ምን ይጠቅማል? የሚል ቢኖር ልሳነ ዕፍረት እንዲህ ያስረዳዋል “ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን።” (ሮሜ. 6:5)።

ሁሉ የራሱ መስቀል አለው ሸክሙን የሚሸከምበት

“ለሁሉም እንዲህ አላቸው፦ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ።” (ሉቃ፣9:23)

ሁሉ የራሱን ሸክም ይሸከማልና

“ወኩሉ ያመክር ምግባሮ (ሁሉ ሥራውን ይመርምር ለሌላው ሳይሆን ለራሱ የሚመካበትን) እስመ ኩሉ ፆሮ ይፀውር (እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሸክም ሊሸከም ነውና)” (ገላ6:5) እንዲል።ስለዚህ የምንሸከመው መስቀላችን የምንሰቀልበት ሳይሆን ሸክማችንን የምንሰቅልበት ነው::”የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ።” (ገላ፣ 5:24) እንደተባለ።

እስኪ አእምሮአችንን ከመባከን ሰብስበን ነፍሳችንን የሚያሳርፍ አንድ ታሪክ እናንብብ

“እርሱም በመንገድ ሲወጣ አንድ ሰው ወደ እርሱ ሮጦ ተንበረከከለትና። ቸር መምህር ሆይ፥ የዘላለም ሕይወትን እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ? ብሎ ጠየቀው።ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም። ትእዛዛትን ታውቃለህ፤ አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥ አታታልል፥ አባትህንና እናትህን አክብር አለው።እርሱም መልሶ፦ መምህር ሆይ፥ ይህን ሁሉ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ አለው።ኢየሱስም ወደ እርሱ ተመልክቶ ወደደውና። አንድ ነገር ጐደለህ፤ ሂድ፥ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ለድሆች ስጥ፥ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ፥ መስቀሉንም ተሸክመህ ና፥ ተከተለኝ አለው።ነገር ግን ስለዚህ ነገር ፊቱ ጠቈረ፥ ብዙ ንብረት ነበረውና እያዘነም ሄደ።” (ማር 10:17)። አይገርማችሁም በምድራችን ላይ ገንዘብን መውደድ የከበደ ሸክም እየሆነባቸው “ገፋኤ-ነዳይ መፍቀሬ- ነዋይ” መጠርያቸው የሆኑ ብዙዎች አሉ:: ፍቅረ ነዋይ (ገንዘብን መውደድ) ለኃጢዓት ሥርና ራስ ነው …… ጌታችን ተርቦ ሳይሳሳ፣ ተፈትኖ ድል ሳይሆን፣ ለሁላችን አርአያ በሆነበት ገዳመ ቆሮንቶስ ጠላታችንን ድል ከነሳባቸው መንገዶች አንዱ ፍቅረ ነዋይን በጸሊዓ ነዋይ ነበር። ይህም ፍቅረ ነዋይ ርዕሰ-ኃጣውእ ከስስትና ከትዕቢት ጋር አርዕስተ ኃጥውእ እየተባለ ይጠራል። ይሁንና ግን ከአስራ ሁለቱ አንዱ በሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ ልብ ገብቶ ተሳካለት። በዚህ ሥፍራ ደግም የኃጢዓት ሥር ተብሎ ተጠራ “ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።” (1ኛ.ጢሞ.6:10) እንዲል። እንግዲህ ይህን የመሰለው ኃጢዓት ሁሉ ክቡድ ሸክም ይባላል። የምሕረት አምላክ ግን በፍቅር ልሳን እንዲህ እያለ ይጠራናል “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።” (ማቴ.11:28-30)።

ቀሊል የሆነውን የእርሱን ሸክም እንሸከም ዘንድ እሱ የኛን ክቡድ ሸክም በመስቀል ላይ ተሸከመ:: እንግዲህ ተመልከቱ በዚህ መንገድ እኛም ሕይወታችንን እንድንሰጠው ሕይወቱን ሰጠን ለምን? የሚል ቢኖር እርሱ የብዙዎችን ኃጢዓት በእንጨት ላይ የተሸከመው ብዙዎች የእርሱን ሕይወት በዘመናቸው እንዲሸከሙ ነውና:: ነቢዩ አስቀድሞ በትንቢት እንዲህ እንዳለ “ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።” (ኢሳ 53:12) ሊቀሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስም የቃሉን መፈስጸም እንዲህ ሲል እንዳስረዳ “ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤” (1ኛ.ጴጥ፣2:24)።

መከራን መቀበል (መስቀላችንን መሸከም)

+ ኃጢዓትን (አርእስተ ኃጣውእ) ያስተዋል።

“በሥጋ መከራን የተቀበለ ኃጢአትን ትቶአልና።” (1ጴጥ፣ 4:2)።

+ ወደ እግዚአብሔር ያስገባል።

“ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል” (ሐዋ 14:22) እንደተባለ ለብዙዎች ዘለፋ የሆነው ይህ የቅዱሳን ሐዋርያት ምስክርነት “በጸጋ ድነናል” እያሉ ባልተገባ ፍካሬ ቃሉን እየጠቃቀሱ፤ ለመብልና መጠጥ ይህን ለመሰለው የሥጋ ፈቃድ ራሳቸውን ለሚያስገዙ ጅራፍ ይሆንባቸዋል፤ ምክንያቱም “የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና።” (ሮሜ.14:17) ይለናልና::
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ::
በዲ/ን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም በጤና ጠብቆ አደረሳችሁ::መልካም የመስቀል በአል ይሁንልዎ:: ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን:: አሜን::

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Dallas?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


1150 Fuller Dr
Dallas, TX
75218

Opening Hours

Sunday 03:00 - 12:00
Other Religious Centers in Dallas (show all)
Church of The Holy Communion Episcopal Church of The Holy Communion Episcopal
17405 Muirfield Dr
Dallas, 75287-7437

Faith Calls Theological Programs for Young People Faith Calls Theological Programs for Young People
5905 Bishop Blvd
Dallas, 75275

We are a faith formation and leadership development program for young people in Christian theological education.

Bible Prayer Fellowship Bible Prayer Fellowship
12104 Josey Ln
Dallas, 75234

We teach Christians to pray with Christ obviously present and actively in charge -- to know God intimately and enjoy the abundant life He gives to those who seek Him.

United MegaCare United MegaCare
3635 Dan Morton Dr
Dallas, 75236

Our mission is to transform and empower lives through hope, practice and partnership. Bring a smile to the face of a child! Support our Toy Drive: http://bit.ly/UMCTD

New Freeman Chapel Missionary Baptist Church New Freeman Chapel Missionary Baptist Church
2219 Lamont Ave
Dallas, 75216

New Freeman Chapel Missionary Baptist Church is a "A New Church with a Vision"

Mercy House - DALLAS TX Mercy House - DALLAS TX
1100 Griffin St W
Dallas, 75215

I woke up this morning with my mind set on Jesus!

Blue Glowcoat LTD Blue Glowcoat LTD
2522 Fort Worth Ave, Apt 306
Dallas, 75211

Harvest Intl Prophetic Ministry Harvest Intl Prophetic Ministry
9606 La Prada Dr.
Dallas, 75228

Non-Denomination prophetic church we believe in prophecy laying on of hands healing's baptism of the Holy Ghost speaking in tongue's .

Shearith Israel Family Center Shearith Israel Family Center
9401 Douglas Ave
Dallas, 75225

Creating strong Jewish families, by connecting home and community.

Frienship-West Baptist Church: Pathfinders Community Frienship-West Baptist Church: Pathfinders Community
2020 W Wheatland Rd
Dallas, 75232

Pilgrim Rest Missionary Baptist Church Pilgrim Rest Missionary Baptist Church
1819 N Washington Ave
Dallas, 75204

WE WALK BY FAITH AND NOT BY SIGHT Sunday Worship Times: 8:00am & 10:45am Sunday School 9:30am-10:30am

Marsalis Ave Church of Christ Marsalis Ave Church of Christ
2431 S Marsalis Ave
Dallas, 75216-2316

Real People Serving the Real God