Kidane Mehret Church

Kidane Mehret Church

Comments

zake matu
ምክረ አበው ቁጥር አንድ
መቅረዝ ዘተዋሕዶ
v ከጐደለን ይልቅ ያለን ይበልጣል፡፡
v ተቀብሎ የማያመሰግን ከቀማኛ ይቆጠራል፡፡
v ለንስሐ የመደብነው ጊዜ ዓለም የማትፈልገውን የዕድሜያችንን ማለቅያ መሆኑ ያሳዝናል፡፡
v ነገሥታት በክርስቲያኖች ጸሎት ካልታገዙ ሰይጣን ሲያውካቸው ሕዝቡን ያውካሉ፡፡
v በጠብ ውስጥ ያለ ረሀብ፣ በድሪቶ ውስጥ ያለ ጥጋብ፣ በጐፈሬ ውስጥ ያለ ጽድቅ አይታወቅም፡፡
v እንደ ዳዊት ስንዘምር እንደ ሜልኮል የሚያሽሟጥጡ አይጠፉም፡፡
v ሰይጣን ላያስተኛን ተኙ ይለናል፡፡
v ማርያም የተመሰገነችው በማርታ ምክንያት ነውና ለማርታም ምስጋና ይገባታል፡፡
v ዝናው ከሥራው በላይ የገነነበት ሰው ያልታደለ ነው፡፡
v ኃጢአቱን ተረድቶ ንስሐ የሚገባ ኃጢአተኛ ምንም በደል ከሌለበት ነገር ግን ራሱን እንደ ጻድቅ ከሚቆጥር ሰው የበለጠ ይሻላል፡፡
v በሽታን እንጂ በሽተኛን አትጥላ፡፡
v ወጣትና ጤናማ ከሆንክ በድካም ለምትሸነፍበት ለእርጅናህ ዘመንም ጭምር ጹም፡፡
v በቻልከው መጠን መንፈሳዊ ሀብትን አከማች፤ በማትችለው ጊዜ ትመነዝረው ዘንድ፡፡
v በብዙ ሰዎች መካከል ተቀምጦ ኅሊናን ባሕታዊ ማድረግ እንዲሁም በብሕትውና ተቀምጦ በሐሳብ በከተማ ውስጥ መኖር ይቻላል፡፡
v ከመጠን በላይ የሚመሰገንና የሚከበር ሰው ብዙ ኩነኔ ያገኟል፤ በሰው ዘንድ ከቁም ነገር ሳይቆጠር መልካም ነገርን ሠርቶ ያለፈ ሰው ግን በሰማይ ታላቅ ክብር ይጠብቋል፡፡
v አንድ መነኰሴ ነበረ፡፡ አስቀድሞ ፍጹም የነበረ ሲሆን በኋላ ግን የትርፋቱን ነገር ቸል አለ፡፡ አንድ ቀንም አባ ኢዮብ ከተባለ ሌላ መነኰሴ ማደርያ ጐጆ ጋር ገባ፡፡ አባ ኢዮብ ያስቀመጠው ምግብንም እስከ መስረቅ ደረሰ፡፡ አባ ኢዮብም ይህንን የስርቆት ተግባር አወቀበት፡፡ ደስ ብሎትም አየው፡፡ አባ ኢዮብ በጊዜ ሞቱ ያን ሰው ጠርቶ እጆቹን ሳማቸው፤ ወደዳቸው፤ እንዲህም አለ፡– “ወንድሜ እኔስ እኒህን እጆችህን እስማቸዋለሁ፤ መንግሥተ ሰማያት የምገባበትን ምክንያት ስላመጡልኝ አመሰግናቸዋለሁ” አለ፡፡ ያም ሌባ መነኰሴ “እንዲህ የሰው መጽደቂያ ሁኛለሁን” ብሎ ንስሐ ገባ፡፡ እግዚአብሔር ይርዳን!!!!!!

Kidane Mehret EOTC in Alexandria, Virginia

THE ROLE OF THE ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH

Operating as usual

08/17/2020
08/16/2020
08/16/2020

Live from kidanemhert church

08/15/2020

Live from kidanmhert church

08/12/2020
08/11/2020
08/10/2020
08/08/2020
08/02/2020
07/28/2020
07/26/2020
07/23/2020

እንኳን ለእመቤታችን የቃል ኪዳን እለት ለኪዳነ ምህረት ወርሃዊ አደረሳችሁ፡፡
Kidist Ebenezer

07/19/2020
07/14/2020

ሐምሌ 7- " በዓለ ቅድስት ሥላሴ+
ወበዛቲ ዕለት ቦኡ ሥሉስ ቅዱስ ውስተ ቤተ አብርሃም ወተሴሰዩ ዘአቅረቦ ሎሙ፡፡ በከመ መጽሐፍ ውስተ ኦሪት ወአብሠርዎ ልደቶ ለይስሐቅ ወባረክዎ፡፡ በዚችም ቀን ልዩ የሆኑ ሦስቱ አካላት /ቅድስት ሥላሴ/ በኦሪት መጽሐፍ እንደ ተጻፈ ወደ አብርሃም ቤት ገቡ ያቀረበላቸውንም ተመገቡ፡፡ የይስሐቅንም ልደት አበሠሩት ባረኩት አከበሩትም፡፡ (መጽሐፈ ስንክሳር ዘሐምሌ ሰባት)

07/05/2020
06/28/2020
06/26/2020

እንኳን ለቅዱስ ገብረኤል ወርሃዊ በዓል አደረሳችሁ፡፡ የእለቱ የኪዳን ፀሎት፡፡

06/21/2020
06/14/2020
06/12/2020
06/07/2020

ይህ አገልግሎት የሚተላለፍላችሁ ከሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ነዉ እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን!!! 🙏

06/04/2020
06/04/2020
06/04/2020
05/31/2020
05/31/2020
05/29/2020

HAMERE NOAH KIDANE MIHRET EOTC

HAMERE NOAH KIDANE MIHRET EOTC
Kidane Mehret EOTC
KMEOTC
KM Church

05/28/2020
kmchurch.org 05/26/2020

KMChurch – Kidane Mhret

የእግዚአብሔር ገንዘብን መስጠት ምስጋና ነው፡፡​
https://www.kmchurch.org//#givingflow&amount=20

kmchurch.org

05/24/2020

ይህ አገልግሎት የሚተላለፍላችሁ ከሐመረ ኖሕ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ነዉ

05/23/2020

ሰላም በምድር

05/21/2020

kidane Mehret Church-ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን-ቨርጂኒያ (KMEOTC)

05/05/2020
09/08/2019
07/07/2019

kidane Mehret Church-ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን-ቨርጂኒያ

እንደሚታወቀው በአሜሪካ በአጠቃላይ በልዩልዩ እስቴቶች በተለይ በዲሲና አካባቢዋ በርካታ አብያተ ክርሲትያናት ተቋቁመው ለምዕመናን ከፍተኛ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ሲሆኑ፤ ከእነዚህም መካከል አንዷ በቭርጅኒያ እስቴት በአሌክሳንድሪያ ከተማ የምትገኘው የሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት፤የሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን የተመሰረተችው በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪ በሆኑት በመላከ ኪዳን ታደሰ ሲሳይና እግዚአብሔር አምላክ በፈቀደላቸው እንዲሁም የኪዳነ ምሕረት ፍቅር ባደረባቸው ምዕመናን እ.ኤ.ዘ አቆጣጠር በየካቲት ወር 1995 ዓ.ም ሲሆን፤ቤተ ክርስቲያኒቱ ከተመሰረተችበት ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፤ሕግና ቀኖናው በሚያዝ በዘው በቃለ አዋዲው መሰረት በሰበካ ጉባኤ ተደራጅታ በመንፈሣዊውም ሆነ በማኅበራዊው ከፍተኛ አገልግሎት በማበርከት ላይ ትገኛለች፤ለበርካትታ ሕፃናት በጥምቀት ልጅነት እንዲያገኙ፤እንዲሁም ምዕመናን ጋብቻቸውን በተክሊልና በቅዱስ ቁርባን እንዲፈጽሙ ሰፊ አገልግሎት የምትፈጽም ከመሆኗም በላይ ጠንካራ የሰንበት ት/ቤት ተቋቁሞ ከፍተኛ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፤ ከዚሁም ጋር ምዕመናን በመድኃኔ ዓለም፤ በእመቤታችን በቅዱሳን ጻድቃንና ሰማእታት በጽዋ ማኅበራት ስም ተደራጅተው መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎታቸውን በማጠናከር ላይ ይገኛሉ፤ ከምታከናውነው መደበኛ አገልግሎት በተጨማሪ በተለይ በጾም ወራት ለሐገርና ለወገን የሚጠቅም የምሕላ ጸሎት ታከናውናለች፤ዘወትር ከምታከናውነው የጸሎት ቅዳሴና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በተለየ ምልኩ በየሳምንቱ ሐሙስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት ትሰጣለች፤በአሁኑ ሰዓት ቤተክርስቲያኒቱ ምንም እንኳ ከተገልጋዩ ምዕመናን አኳያ ሲታይ በቂ ባይሆንም የራሷ የሆነ ቤትና ቦታ ገዝታ አገልግሎቷን በማበርከት ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ራሱን የቻለ ሰፊ የሆነ ለክርስቲያን የሚሆን ቤትና ቦታ ለመግዛት በከፍተኛ ጥረት ላይ ትገኛለች፤ቤተ ክርስቲያን ማለት የማኅበረ ምእመናን ስብስብ ሲሆን በሌላም አነጋገር ክርስቲያኖች የሚሰበሰቡበት ልዩ ስብሐት እግዚአብሔር የሚቀርብበት፤መስዋዕት የሚሰዋበት ልዩ ቦታን ያሳያል፤ እንግዲህ ቤተ ክርስቲያናችንን ስንምለከታት እዝል ቅፅል የሌለባት ቀዳማዊት፤ ሐዋርያዊትና፤ብሔራዊት በክርስቶስ ፤ደም፤በሐዋርያት መሰረት ላይ የታነጸች የተመሰረተች ወልድ ዋሕድ በማለት ፀንታ የኖረች፤የምትኖር ከኦሬንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዷ የኛዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት፤ይህች ጥንታዊት ፤ ሐዋርያዊትና ብሔራዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ሐገራችን በመንፈሳዊም ሆነ በማኅበራዊ ከፍተኛ አገልግሎት ከማበርክቷም በላይ ዳር ደንበሩ እሳት መካከሉ ገነት ተብሎ እንዲነገርላት ያደረገች በፍጹም እምነት: ሃይማኖቷን አጥብቃ በመያዝ በምታደርሰው ጸሎትና በምታቀርበው መስዋዕት እንደሆነ በሁላችንም ኢትዮጵያውያን ዘንድ ግልጽ ነው፤ ሕዝቧም ፤ የባዕድ ሥራዓተ ማህበር መጥቶ የመውደቅ የመነሳት ታሪክ ቢአጋጥመውም በዓለም መድረክ ቢናገር የሚሰማ፤ የሚደመጥ፤ ቢጠይቅ መልስ የሚያገኝ ፤ሐገር አኩሪ፤ ወገን አስከባሪ፤ አገሩን አፍቃሪ ፤ ለወገኑ ተገን ፤ ታላቅ ሕዝብ እንደሆነ ታሪክ ምስክር ነው፤የእምነት የለሽ ሥራዓት ማህበር ወደ ሐገራችን ተጭኖ ሲገባ የሕዝቦቿን አምልኮታዊ ባሕርይ የሚለወጥ፤ የብዙ ዘመናት ሥራዓትና ወጉን የሚያናጋ፤ ሐገሪቱን የታሪክና የባሕል አልባ በማድረጉ ይህ ታላቅና ኩሩ ሕዝብ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ሳይወድ በግድ ሀገሩን ልቆ እንዲሰደድ ሆነ በመሆኑም በዓለም ዙሪያ እንደ ጨው ተዘርቶ ይገኛል ፤ይሁን እንጅ በተሰደደበት ቦታ ሁሉ ፤ ባሕላዊ ምግቡን እንጀራ ወጡን፤ ባሕላዊ ልብሱን ጥበብ ኩታውን፤ ሥራዓቱን ወጉንና ሃይማኖቱን በመጠበቅ እንደሚታወቀው ሐገሩንና ባሕሉን በማስተዋወቅ ላይ ሲሆን እምነትን በተመለከተም ‘’በአለህበትና በሄድክበት ቦታ ሁሉ እግዚአብሔር አምላክህን በፍፁም ነብስህ በፍፁም ሐሳብህ በፍፁም ኃይልህ ውደድ ያለውን አምላካዊ ቃል ተግባራዊ በማድረግ በስደቱ ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሁሉ አምልኮተ እግዚአብሔር ለሚፈጸምበት ቅድሚያ በመስጠት ቤተ ክርስቲያናቸውን በመመሥረት እምነታቸውንና ሥራዓተ አምልኮታቸውን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፤

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የወደፊት የቤተክርስቲናችን ዕቅዷም የሚከተሉት ናቸው፤

ሰፊ የሆነ ለክርስቲያን የሚሆን ቦታ በመግዛት ቤተክርስቲያኒቷን ከማስፋፋት ጋር፤-1ኛ.የምግባረ ሰናይ የሴቶች ማኅበር ማቋቋም2ኛ.የተለያዩ የቤተክርስቲያን የአብነት መምህራንን ማለት የቅዳሴ፤የዜማ፤የቅኔ፤የመጽሕፍት ወዘተ የመሳሰሉትን በማስመጣት ስብከተ ወንጌል እንዲስፋፋ፤ ለወጣቱና ለተተኪው ትውልድ የቤተክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ ትምህርት እንዲማርና አገሩንም ቤተክርስቲያኒቱንም እንዲያውቅ ማድረግ፤3ኛ የአጸደ ህጻናት ትምህርት ቤት መክፈት4ኛ የካህናት መኖሪያና የእንግዳ መቀበያ እንዲኖር ማድረግ5ኛ በእድሜ ፤በሕመም፤ በልዩልዩ ምክንያት እራሳቸውን መርዳት ለማይችሉ ኢትዮጵያውያን መጠለያ እንዲኖር ማድረግ ሲሆን፤ እነዚህን የታቀዱ ዕቅዶች ተግባራዊ ለማድረግ የሚቻለው የሁሉም ኢትዮጵያዊ ተሳትፎና ድጋፍ ሲጨመርበት ስለሆነ ሐብት ያለው በሐብቱ ፤ ሐብቱ የሌለው በጉልበቱ በእውቀቱ ትልቅ ትንሽ ሳይባል በመረዳዳት ለታቀዱ ሥራዎች ተግባራዊነት ሁላችንም እንድንረባረብ በቤተክርስቲያናችን ስም እንጋብዛለን፤

እግዚአብሔር አምላክ ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ሰላሙን፤አንድነቱንና መግባባቱ ይስጥልን ይህንን የምንኖርበትን ምድረ አሜሪካን በጸጋው በቸርነቱ ይጠብቅልን ለ እኛ ለሁላችንም የአምላካች ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፤ አሜን

Videos (show all)

Live from kidanmhert church
እንኳን ለእመቤታችን የቃል ኪዳን እለት ለኪዳነ ምህረት ወርሃዊ አደረሳችሁ፡፡ Kidist Ebenezer

Location

Telephone

Address


75 S Bragg St
Alexandria, VA
22312
Other Religious Centers in Alexandria (show all)
Christian Science Reading Room - Alexandria VA Christian Science Reading Room - Alexandria VA
691 S Washington St
Alexandria, 22314

The Reading Room is a combination library, bookstore and study center with Bible study materials and writings on Christian Science.

Epiphany Lutheran Church of Mount Vernon Epiphany Lutheran Church of Mount Vernon
5521 Old Mill Rd
Alexandria, 22309

We're an ELCA congregation in historic Mount Vernon, Virginia. We worship at 9:30 a.m. on Sundays (right now only online) including here on this page. We are a Reconciling in Christ congregation where everybody is welcome and fully included.

Saint Louis Catholic Church Saint Louis Catholic Church
2907 Popkins Ln
Alexandria, 22306

Harvest Intercontinental Church - Virginia Harvest Intercontinental Church - Virginia
8305 Richmond Hwy, Suite 2A
Alexandria, 22309

Harvest Intercontinental Church - Virginia is a multicultural, missions-oriented, and disciple-making church located in Alexandria, Virginia.

Mount Vernon Presbyterian Church Preschool Mount Vernon Presbyterian Church Preschool
2001 Sherwood Hall Ln
Alexandria, 22306

Heritage Presbyterian Church, Alexandria, VA Heritage Presbyterian Church, Alexandria, VA
8503 Fort Hunt Rd
Alexandria, 22308

A warm and friendly neighborhood church, Connecting with God and our neighbors through worship and fellowship, Growing in Christ, and Serving our Lord locally and through global missions.

Beverley Hills Community United Methodist Church Beverley Hills Community United Methodist Church
3512 Old Dominion Blvd
Alexandria, 22305

As the first Reconciling Congregation in Northern Virginia, we welcome all people as they are with the aim of growing together in faith and fellowship and sharing Christ-like love.

Full Gospel First Church of Washington English Ministry Full Gospel First Church of Washington English Ministry
6401 Lincolnia Rd
Alexandria, 22312

6401 Lincolnia Road, Alexandria, Virginia

Old Town Community Church Old Town Community Church
212 S Washington St
Alexandria, 22314-3626

Old Town Community Church - Bringing hope to Old Town through the truth of an timeless faith.

Iglesia de Dios"El Sinai" Iglesia de Dios"El Sinai"
3421 Franconia Rd
Alexandria, 22310

Este portal a sido creado con el proposito de dar conocer las buenas nuevas de Jesucristo a toda la humanidad.

Antsokia Ethiopian Evangelical Church Alexandria, VA Antsokia Ethiopian Evangelical Church Alexandria, VA
1400 Russel Rd
Alexandria, 22301

- Antsokia Ethiopian Evangelical Church in Alexandria VA, USA Come; experience the presence of the Lord Jesus in a mission centered and multiplying church