The Church of the Resurrection Power of Jesus in Paris

የትንሳኤው ሃይል ቤተክርስትያን-ፈረንሳይ ቤተክርስትያናችን በሜይ 30/2019 በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ ተመስርታ የመጀመርያው መንፈሳዊ ፕሮግራም እሁድ ጁን 2/2019 ተካሂዶአል። ቤተክርስትያኒቱ ፔንቴኮስታል (Pentecostal) ቤተክርስትያን ስትሆን ከተለያዩ ሌሎች ቤተክርስትያናት ጋር በወንጌል አብሮ በመስራት የምታምን ናት። መልእክተኝነታችን (አላማችን) አንድና ብቸኛ በሆነው በኤፌሶን 1፥9-10 በተጠቀሰው አለምን በክርስቶስ መጠቅለል በሚለው የእ/ር ራእይ ውስጥ የክርስቶስ ህይወትና የትንሳኤውን ሃይል መግለጥ ነው። ተልእኮ (Mission) 1. አማኞች በእ/ር ቃል የታነጹ እንዲሆኑ መሰረታቸውን የሚያጸኑ ትምህርቶችና ስብከቶችን መስጠት፣ 2. ክርስቶስን መምሰል ማእከል ያደረጉ ትምህርቶችንና ስብከቶችን መስጠት፣ 3. አማኞች የእ/ርን ፈቃድ አውቀው የህይወታቸው መርህ እንዲያደርጉት ማነጽ፣ 4. አማኞች በሚኖሩበት ማህበረሰብ ውስጥ የክርስቶስ ደቀመዝሙር ሆነው ተጽእኖ ፈጣሪ እንዲሆኑ ማነጽ፣ 5. አማኞች የክርስትና እሴቶችን:- እምነትን፣ ፍቅርን፣ ጸድቅን፣ ቅድስናን ፣ እ/ር መፍራትን እርስ በእርሳቸው እንዲያሳዩ ማነጽ፣ 6. የክርስትና የክብር ህይወት በአማኝ ህይወት ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ እንዲገለጥ ማነጽ፣ 7. በመንፈስ ቅዱስ የጸጋ መገለጥ በፈውስ ፣ ሃይልን በማካፈል፣ በነጻ ማውጣት ማገልገል፣ 8. ለማያምኑ የክርስቶስን ወንጌል መመስከር፣ የእምነት አቋም 1. መጽሃፍ ቅዱስ 66ቱን የብሉይና የሐዲስ ኪዳን ቅዱሳት መጻሕፍት ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ የጻፉትና ሙሉ ስልጣን ያለው የህይወታችን መመርያ እንደሆነ እናምናለን፡፡ 2. በአንድ አምላክ፣ በሶስት አካል እና በሶስት የመገለጥ ስርዓት እናምናለን፡፡ በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ በስላሴ እናምናለን፡፡ 3. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር አንድያ ልጅ መሆኑን ፣ ከድንግል ማርያም መወለዱን ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑን እናምናለን፡፡ 4. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ቤዛ ሆኖ በመስቀል ላይ መሞቱን መቀበሩንና በሶስተኛው ቀን በአካል ከሙታን መነሳቱን ወደ አብ ቀኝ ማረጉንና አሁን ለእኛ እንደሚማልድ ደግሞም በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ እንደሚመለስ እናምናለን፡፡ 5. ሰው በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠሩን ፣ ሆኖም በሃጢአት በመውደቁ ምክንያት የእግዚአብሔር ቁጣና ፍርድ ያለበት በደለኛ መሆኑን እናምናለን፡፡ 6. ሰው ከሃጢአት ሃይልና ቅጣት ሊድን የሚችለው ሃጢአት የሌለበት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ምትክ ሆኖ በፈጸመው የቤዛነት ስራ ብቻ በመሆኑ ሰው በእግዚአብሔር ፀጋ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ እንደሚጸድቅ እናምናለን ፡፡ 7. በሃጢአት ምክንያት ወደ ሰው ህይወት በሽታ፣ ጭንቀት ፣ ፍርሃት፣ ሞት፣ ፍሬያማ ያልሆነ ህይወት፣ ተስፋ መቁረጥ እና ሌሎች ከጨለማ አለም የሆኑ ስርአቶች ገብተውበታል፡፡እነዚህ ሁሉ በክርስቶስ የመስቀል ስራ እንደተሻሩና በእምነት በነፃነት መኖር እንደሚቻል እናምናለን፡፡ 8. ሰው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ዳግመኛ ሲወለድ አዲስ ፍጥረት እንደሚሆን መንፈስ ቅዱስ በሕይወቱ እንደሚሰራ እናምናለን ፡፡ 9. ሰው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ንሰሐ በገባ ጊዜ በክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ መተባበሩን ለመግለጽ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በውሃ ውስጥ በመጥለቅ እንዲጠመቅ እንዲሁም ጌታ እስኪመጣ ሞቱን ለመናገርና ከምዕመናን ጋር ያለውን ሕብረት ለመግለጽ የጌታን እራት እንደሚካፈል እናምናለን:: 10. መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ሕይወት ውስጥ እንደሚኖር እናምናለን:: አማኙ በመንፈስ ቅዱስ ሲጠመቅ ሃይልን እንደሚቀበልና በልሳን እንደሚናገር በየጊዜውም በመንፈስ ቅዱስ እንደሚሞላ እናምናለን፡፡ 11. በቤተክርስትያን አንድነትና በክርስቶስ አካልነቷ እናምናለን፡፡ 12. በክርስቶስ ዳግም ምፅዓትና በትንሳኤ እናምናለን ፣ ይህ አለም እንደሚያልፍና አዲስ ሰማይና ምድር ለአማኝ እንደተዘጋጀ እናምናለን ፡፡ 13. የመንፈስ ቅዱስ የፀጋ ስጦታዎች ሁሉ እስከ ክርስቶስ ምፅዓት ድረስ እንደሚሰሩ እናምናለን፡፡

Fonctionnement normal

ሻሎም ወገኖች። እሁድ ኦገስት 16/2020 ከቀኑ 15:00-19:00 ሰአት "መንፈስ ቅዱስና ተልእኮው" በሚል ሃሳብ በቤተክርስትያናችን የአንድ ቀን ልዩ ፕሮግራም ተዘጋችቶአል። ፓስተር አንተነህ ከስዊዘርላንድ ያገለግለናል። በዚህ የአምልኮ የትምህርትና የጸሎት ፕሮግራም ላይ እንድትካፈሉ በፍቅር ተጋብዛችኋል።

ወደ መደበኛ የቤተክርስትያን ፕሮግራማችን ተመልሰናል።
አብራችሁን እንድትካፈሉ እንጋብዛችኋለን።
በቤተ ክርስትያናችን አድራሻ
ዘወትር እሁድ ከ15:00-18:00 የአምልኮ፣ የጸሎትና የቃል ግዜ
የZoom አገልግሎት
ዘወትር እሮብ የጸሎት አገልግሎት
ከ19:00-21:00 ሰአት
ዘወትር አርብ የመጽሃፍ ቅዱስ ጥናት ግዜ
ከ19:00-21:00 ሰአት

እሁድ ፌብሩዋሪ 16/2020 የኮንፍረንሳችን መዝጊያ ላይ ጌታ እጅግ ድንቅ ግዜን ከፓስተር ውብሸት ጋር ሰጠን። "የእ/ር ሃይል" በሚል ሃሳብ የእ/ር ቃል በስልጣን የተሰበከበት፣ ከሰዎች ላይ የተለያዩ የአጋንንት ምሽጎች(strongholds) የተሰበሩበት ፣ የጌታ እጅ የታየበት ልዩ ግዜ ነበር። እ/ር ህዝቡን ጎብኝቶአል። ክብር ሁሉ ለጌታ ይሁን !!!

ትናንት ቅዳሜ ፌብሩዋሪ 15/2020 በኮንፍረንሳችን የመጀመርያ ቀን "መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ህይወት ውስጥ " በሚል ሃሳብ ድንቅ ግዜ ነበረን። ከፍ ባለ የመንፈስ ቅዱስ ህልውና ውስጥ ነጻ መውጣት፣ ቀንበር የመስበርና ሃይል የመካፈል ግዜ ነበር። ክብር ለጌታ ይሁን ! ዛሬም ኮንፍረንሳችን ከ15:00-19:00 ሰአት ይካሄዳል። ሁላችሁም ተጋብዛችኋል !

ፌብሩዋሪ 15 እና 16/2020 Focus International Ministry ከትንሳኤው ሃይል ቤተክርስትያን -ፓሪስ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መንፈሳዊ የመነቃቂያ ፕሮግራም ላይ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
አድራሻ:- 36 rue du Borrego, 75020 Paris.
ከ 15:00-19:00 ሰአት
በሁለቱም ቀናት:-
ለፈውስ፣ ለነጻ መውጣት፣ ለመንፈስ ቅዱስ ሙላትና ሃይል ለመካፈል ይጸለያል።

እሁድ ዲሴምበር 15/2019 በነበረን ልዩ የመነቃቂያ ፕሮግራም ላይ ጌታ ከፓስተር ውብሸት ( ከUSA) እና ዘማሪ ወንድወሰን (ከHoland) ድንቅ የሆነ ግዜን ሰጠን። ከፍተኛ የትራንፖርት ችግር የነበረ ቢሆንም ሁኔታው ሳይገድባቸው የተገኙ ሁሉ የእ/ር ህልውና እና ሃይል አግኝቶአቸዋል። የእ/ር ቃል ( ኢሳ 61፥1-3) ከፍ ባለ የመንፈስ ጉልበት ተሰብኮአል። በጸሎት አገልግሎት ሰዎች ከተለያየ የአጋንንት እስራት ተፈተዋል። ክብር ሁሉ ጌታ ይሁን !!!

እሁድ ዲሴምበር 15/2019 Focus International Ministry ከትንሳኤው ሃይል ቤተክርስትያን -ፓሪስ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መንፈሳዊ የመነቃቂያ ፕሮግራም ላይ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
አድራሻ:- 36 rue du Borrego, 75020 Paris.
ከ 15:00-19:00 ሰአት
የፈውስ፣ የነጻ መውጣትና የሃይል የመካፈል ፕሮግራም።

The Church of the Resurrection Power of Jesus in Paris's cover photo

The Church of the Resurrection Power of Jesus in Paris's cover photo

[06/02/17]   መዝሙር ም1

1.ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥
በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥
በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ።

2. ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል።

3. እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።

[02/02/17]   የእሁድ ጃንዋሪ 29/2017 ጉባኤ። God is a Person የትምህርት ክፍለ ግዜ።
~ እግዚአብሄርን እንደ Person ካላወቅነው ግምትና ሃይማኖት ይሆንብናል።
~ የ person ዋነኛ መለኪያው" ፈቃድ" የሚባለው ነው።
~ ትክክለኛ እምነት ከፈቃዱ እውቀት የሚጀምር ነው። ባልተገለጠ ፈቃዱ ውስጥ እግዚአብሄርን ልታውቀውና ህብረት ልታደርግ አትችልም።
~ እግዚአብሄር አሁን ላንተ ያለው ፈቃድ ካንተ ሁኔታ አይጀምርም።
~ ክርስቶስ የእግዚአብሄር ፈቃድ መገለጥ ነው።
~ ፈቃዱ እንደማይለወጥ ሊያታውቀን ስለወደደ በሁለት ነገር አትሞታል ( ክርስቶስ በሰማይ ሰለአንተ ይታያል ፣ መንፈስ ቅዱስ በዚህ የርስትህ መያዣ ሆኖ ተሰጥቶሃል)።
~ ፈቃዱን ካወቅን በኋላ ሃይሉን መለማመድ አለብን ( መዝ 110:2):። ሃይል የመለኮት ባህርይ ነው ( ሮሜ 1:20)። ሃይል "የማድረግ ብቃት" ነው።ፈቃድ የሚፈጸመው(የሚከናወነው) በፈቃዱ ባለቤት ሃይል መጠን ነው። በመለኮት የፈቃድ አሰራር የሚሄድን ሰው የመለኮት ሃይል ይደግፈዋል ። ለምን ቢባል የጌታ ሃይል የሚሰራው ፈቃዱን ለመፈጸም ነው ( ኤፌ1:11).
~ ያመንከውን ወደ ውጤት ማምጣት የምትፈልግ የውጤት ሰው ከሆንክ የጌታን ሃይል ባንተ እንደሚሰራ ማረጋገጥ አለብህ ( ኤፌ3:20).....ይቀጥላል።

Vous voulez que votre lieu de culte soit Lieu De Culte la plus cotée à Paris?

Cliquez ici pour réclamer votre Listage Commercial.

Emplacement

Téléphone

Adresse


36 Bis Rue Du Borrégo
Paris
75020

Heures d'ouverture

Mercredi 18:00 - 20:00
Dimanche 15:00 - 18:00
Autres Églises pentecôtistes à Paris (voir toutes)
UPC Paris Centre UPC Paris Centre
14 Rue De Patay
Paris, 75013

Paris Centre Church is an Apostolic Pentecostal Church made up of people from varying nationalities, cultures and backgrounds, and with a common goal of promoting the Gospel of Jesus Christ. Our services are in English and French.