St. George Ethiopian Orthodox Tewahedo Church-Brisbane Australia

St George Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in Brisbane Australia. Established in 2010....

St George Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in Brisbane Australia. Established in 2010, the St. George's Ethiopian Orthodox Church has been serving the Brisbane Ethiopian Orthodox community and surrounding cities for over 4 years. 1. To expand the words of God according to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church doctrine and teachings. 2. To provide the congregation with quality sacramental and liturgical services. 3. To construct/buy a new church building, this can accommodate bigger congregation

Hara Tewahido ሐራ ተዋሕዶ

በሰሞኑ ጥቃት ለተጎዱ ምእመናን የ2 ሚሊዮን ብር ጊዜያዊ ድጋፍ ይደረጋል፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ልኡካን ተጎጂዎችን እያጽናኑ ነው

• በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጉባኤው ወሰነ፤
• የአደጋ መከላከል እና የሕዝብ ግንኙነት ኀይለ ግብር ይቋቋማል፤
• የሰማዕታተ ሊቢያን ዐፅም ወደ ሀገር ለማምጣት እየተሠራ ነው፤
***

ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ ከተሞችና አካባቢዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች ለተጎዱ ምእመናን፣ የኹለት ሚሊዮን ብር ጊዜያዊ ርዳታ እንዲደረግ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የወሰነ ሲኾን፣ የተመደቡ ብፁዓን አባቶች የማጽናናት ተልእኳቸውን ጀምረዋል፡፡

ካለፈው ጥቅምት 12 እስከ 15 ቀን፥ በምሥራቅ ሐረርጌ ጎሮ ጉቱ ወረዳ፣ በምዕራብ አርሲ-ዶዶላ እና ኮፈሌ፣ በባሌ ሮቤ እና ድሬዳዋ፣ የብሔርና የሃይማኖት አክራሪዎች ካደረሷቸው አሠቃቂ ግድያዎች ባሻገር፣ የምእመናንን መኖርያ ቤቶች፣ ልዩ ልዩ ንብረቶችና የንግድ ተቋሞች፣ ሙሉ በሙሉ በመዝረፍና በማቃጠል የተነጣጠረ ጥቃት ፈጽመዋል፡፡ በዚህም፣ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ምእመናን ከቀዬአቸው ተፈናቅለው፣ በአብያተ ክርስቲያንና በሌሎች ጊዜአዊ መጠለያዎች ለመሰንበት ተገደዋል፡፡

በዶዶላ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረ ክርስቶስ እና ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን፣ ከ4ሺሕ400 በላይ የኾኑ ምዕመናን ከቤተ ሰቦቻቸው ጋራ ተጠልለው ይገኛሉ፤ የወረዳው ቤተ ክህነት ጽ/ቤት፣ መኖርያ ቤቶቻቸው፣ ልዩ ልዩ ንብረቶቻቸው፣ የንግድ ተቋሞቻቸውና ድርጅቶቻቸው በአክራሪዎቹ የተዘረፉባቸውንና በቃጠሎ የወደሙባቸውን ከ133 ያላነሱ ምእመናን ዝርዝር በሪፖርት አስታውቋል፡፡

በምሥራቅ ሐረርጌ ጎሮ ጉቱ ወረዳ መንዲሳ ቀበሌ ጋንጌሶ፣ ዴራ እና ቡራክሳ ጎጦች እንዲሁም በካራሚሌ እና ባሮዳ፣ ከ149 በላይ አባወራዎች ንብረት ሙሉ በሙሉ ተዘርፏል፤ መኖርያ ቤቶቻቸው ተቃጥሎ ለእንግልትና መፈናቀል ተዳርገዋል፡፡ በድሬዳዋ የተፈናቀሉ ምእመናን በቤተ ክርስቲያንና በትምህርት ቤት ተጠልለው እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ አንድ ሚሊዮን ብር፣ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አንድ ሚሊዮን ብር ወጪ ኾኖ የኹለት ሚሊዮን ብር አስቸኳይ ርዳታ እንዲደረግላቸው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ባለፈው ሳምንት ወስኗል፤ በዘላቂነትም ተጎጂዎችን ለማቋቋም የሚያስችል የተጠና ድጋፍ፣ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ በሚያቋቁመው ኮሚቴ በኩል እንዲከናወን መመሪያ ሰጥቷል፡፡

በምልአተ ጉባኤው የተመደቡ ሦስት ብፁዓን አባቶች፣ ትላንት እሑድ ጥቅምት 23 ቀን፣ በዶዶላ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረ ክርስቶስ እና ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በመገኘት የማጽናናት ተልእኳቸውን ጀምረዋል፡፡

በምዕራብ አርሲ-ሻሸመኔ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኄኖክ የተመራው ልኡኩ፣ የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ እና የሶማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የሚገኙበት ሲኾን፣ የልዩ ልዩ መምሪያ ሓላፊዎችንና የሀገረ ስብከቱን ሓላፊዎች ያካተተ ነው፡፡ በዶዶላ ቆይታው፣ ምእመናኑን በማጽናናት የምግብ እና የቁሳቁስ ልገሳ አድርጓል፡፡

በቀጣይም ይኸው የቅዱስ ሲኖዶስ ልኡክ፣ በባሌ ሮቤ እና ሌሎች ጉዳት ወደደረሰባቸው አካባቢዎች ተዘዋውሮ የማጽናናት እንዲሁም አስፈላጊውን ርዳታ የመስጠት ተግባራትን ያከናውናል ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል፣ ለወቅታዊ ችግሮች አስቸኳይ መፍትሔ የሚያፈላልግና ተጓዳኝ የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎችን የሚሠራ ኮሚቴ፣ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ሥር በመምሪያ እንዲቋቋም ምልአተ ጉባኤው መወሰኑ ታውቋል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት በየአካባቢው በሚከሠቱ ተቃውሞዎች፣ ቤተ ክርስቲያን ተከታታይ እና ቋሚ የብሔርና የሃይማኖት አክራሪዎች ጥቃት ዒላማ ከመኾኗ ጋራ በተያያዘ፣ የጥቃት መከላከል እና የኮሚዩኒኬሽን ኀይለ ግብሮች በምልአተ ጉባኤው እንዲቋቋሙ፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በስብሰባው የመክፈቻ ቃለ ምዕዳናቸው ቅዱስ ሲኖዶሱን መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡

ዋናው ጉዳይ ውሳኔውን ተግባራዊ የማድረግ ኾኖ እንጂ፣ ምልአተ ጉባኤው፣ የጥቃትና አደጋ አዝማሚያዎችን በማጥናትና በመተንተን አስቀድሞ ለመጠንቀቅ፣ ለመዘጋጀትና ፈጥኖ ለመከላከል የሚያስችል አካል እንዲቋቋምና ሥርዐቱም እንዲዘረጋ ወስኖ መመሪያ የሰጠው፣ በጥቅምት 2011 ዓ.ም. መደበኛ ምልአተ ጉባኤው እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም፡፡

በተያያዘ ዜና፣ በሚያዝያ ወር 2007 ዓ.ም. በአይ ኤስ ዓለም አቀፍ የሽብር ቡድን፣ በሜዲትራንያን የባሕር ዳርቻና የሊቢያ በረሓ፣ በሰይፍ ተቀልተውና በጥይት ተደብድበው ሰማዕትነትን የተቀበሉ 28 ኢትዮጵያውያን ሰማዕታትን ዐፅም ወደ ሀገር ለማምጣት ጥረቱ እንደቀጠለ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ላይ ተገልጿል፡፡

“ስለ ሰማዕታተ ሊቢያ ዐፅም ጉዳይ” በሚል በተያዘው አጀንዳ ላይ እንደተገለጸው፣ የሰማዕታቱ ዐፅም በጅምላ የተቀበረበት ቦታ ተለይቶ መታወቁን፣ ወደ ሀገር ቤት በሚመጣበት ኹኔታ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋራ ንግግር እየተደረገ እንደኾነ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ “መሥመር ይዟል፤ እንዴትና መቼ ይምጣ የሚለውን እየመከርንበት ነው፤” ብለዋል አንድ የምልአተ ጉባኤው አባል፡፡

ሃይማኖታችንን አንክድም ብለው ስለ ሃይማኖታቸው የተገደሉት 28ቱ ወጣቶች፣ የሃይማኖት መስተጋድላን በመኾናቸው የሰማዕትነት ክብር እንደሚገባቸው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. ባደረገው የርክበ ካህናት ምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

Ethiopian DJ የኢትዮጵያ ሙዚቃ

“የኢትዮጵያ መንግሥት ስብከቱን ትቶ ስራዉን ይስራ÷ ስብከቱን እኛ እንሰብከዋለን” Abune Erimas
በእውነት ደስ የሚል መልክት ነው ቃለህይወት ያሰማልን እረጅም እድሜ ከጤናጋር ይስጥልን በረከታቹ ይደርብን

አንድ ጠንካራ የፖለቲካ ድርጅት ሳይኖር
የኢህአዴግ መፈረካከስ አደጋ ነው ለሀገር
አቡነ ኤርምያስ በግሸን ደብረ ከርቤ

This is Christian Assyria

Stop Burning Ethiopian Orthodox Tewahido Church!

This is Christian Assyria

A demonstration in northern partes of Ethiopia against the attacks on the Ethiopian Orthodox Church

ቄስ በላይ የሲኖዶስ ውግዘት ጥሶ መንግሥት በፈቀደለት አዳራሽ መግለጫ እየሰጠ ነው።

~ ~ የሲኖዶሱ ውገዘት ተጥሷል።
በላይ መኮንንም መግለጫ እየሰጠ ነው።
*★★★*

★ እኔ ግን በጣም ደስ ብሎኛል። ጳጳሳቱም፣ ኦርቶዶክሳውያኑም ምንም አያመጡም። ዝም ብለህ ቀጥል ብለው እነ ታከለ ኡማ መፍቀዳቸው አስደስቶኛል።

#ETHIOPIA | ~ ፕሮቴስታንትና የወሃቢይ መሪዎቻችን ኦርቶዶክስን አቃጥለውም፣ ከፋፍለውም ካላፈረሷት እንደማይተኙልህ እወቅ።

•••
የኦህዴድኦነግ መንግሥትም ለውጉዛኑ አዳራሽ ፈቅዶ በመስጠት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያለውን ንቀት በግልፅ አሳይቷል።

•••
• ዐቢይ አህመድ እስላምና ኦሮሞና ፕሮቴስታንት።
• ለማ መገርሳ ኦሮሞና ፕሮቴስታንት።
• ሽመልስ አብዲሳ ኦሮሞና ፕሮቴስታንት።
• ታከለ ኡማ ኦሮሞና ፕሮቴስታንት።
• ጃዋር መሃመድ ኦሮሞ እስላምና ፕሮቴስታንት።
• ደመቀ መኮንን እስላምና ፕሮቴስታንት።
• ሙፈሪያት ካሚል ኦሮሞ ስልጤና እስላም። ሌሎቹም እንደዚያው። ከባለሥልጣናት ኦርቶዶክሳውያን ሃባ የሉም። የነበሩትም ሰኔ 15 ተረሽነዋል።

•••
ታከለ ኡማም ፓትሪያርኩን አሞኝቷቸዋል። የሰላም ሚንስትሯም አባ ማትያስን ሸውዳቸዋለች። አሁን ነገሩ እየጠራና ግልፅ እየሆነ መጥቷል። ይኸው ነው ወዳጄ። ባለቤቷን የተማመነች በግ ላቷን ከጋጣው ውጭ ታሳድራለች ነው ነገሩ። እንግዲህ በቀጣይ የሚሆነውን አብረን መጠበቅ ነው።

•••
የቤተ ክህነቱ መግለጫ ላይ ራዲዮ ፋናና ኢቲቪ እንዳይገኙ የተደረገው ለምን ይመስልሃል? አሁን የገጠመን ነገር ከዛሬ 500 ዓመት በፊት ከገጠመን ፈተና የከፋና የባሰ ነው አለ አሳምነው ጽጌ። ነፍስህን ይማረው።

★ በቀጣይ ዋቄፈታና እነ በላይ ደብረ ሊባኖስ የእኔ ነው የእኔ ነው ብለው በመጣላት ወደ ፍርድ ቤት ያመሩልሃል። ዳኛው ኦቦ መገርሳና ሼክ አብዱረሃማን ነው። ያው ለዋቄፈታዎቹ ይፈርድላቸውና ደብረ ሊባኖስን በቁሙ ያወርስልሃል። ቱ ምን አለ ዘመዴ በለኝ። ጠብቅ።

• የህንድ ኦርቶዶክስ ፈተና በኢትዮጵያም በቅርቡ ይደገማል። የሲኖዶሱ አባላት ፈሪዎችና የካድሬዎች ስብስብ ስለሆነ በዚያ በኩል እንዲያው ድንገት ተአምር ካልተፈጠረ በቀር ብዙም እምነትና የምጠብቀው ነገር የለኝም።

•••
የፓትሪያርኩ አማካሪ የሊቀ ዘማውያን ትዝታው ሳሙኤል ጓደኛ አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ከአክሱም ሆነው ቄስ በላይ ያመጣው ሃሳብ ትክክል ነው ሲሉ ስታይ ይሄ እኩይ ተግባር የማን ሥራ እንደሆነ ወለል ብሎ ይታይሃል። ሲኖዶስ ተንቋል። ቤተ ክርስቲያን ተደፍራለች፣ ተዋርዳለች።

•••
ጀግና ጀግና የተባሉት ጳጳሳት በራሱ ድራሻቸው ጠፈፍቷል። ካሴትና መጽሐፍ ቸርቻሪው ሰባኪ ነኝ ባዩ ሁላ እናቱ ቀሚስ ስር ተወሽቋል። እናም እነ በላይ በግልጽ ከቤተ ክርስቲያን አፈንግጠው መውጣታቸውን በግልጽ አውጀዋል።

•••

ሻሎም ! ሰላም !

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ነሐሴ 26/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።

እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ደገኛው የሰላም አባት ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ዐረፉ

ደገኛው የሰላም አባት ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ዐረፉ

• ሥርዐተ ቀብሩ ቅ/ሲኖዶስ በሚወስነው ቀን በመካነ ሰማዕት ቅ/ገላውዴዎስ ይፈጸማል፤
• ለ41 ዓመታት፣ ከኤጲስ ቆጶስነት እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊነት አገልግለዋል፤
• ከማሕሌት እስከ ዐውደ ምሕረት፣ በሙሉ የአገልግሎት ትጋታቸው ይታወቃሉ፤
• በኹለት ቅዱሳን ፓትርያርኮች ምርጫ ወቅት በዕጩነት ቀርበዋል፤
***

ከሊቅነትና ከደግነት ጋራ በተሟላ የአገልግሎት ሕይወታቸው የታወቁት፣ አንጋፋው የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ዐረፉ፡፡

የ84 ዓመቱ አረጋዊ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ ዛሬ ቅዳሜ፣ ግንቦት 17 ቀን 2011 ዓ.ም.፣ 11፡30 ላይ፣ ከስኳር እና ከልብ ሕመም ጋራ በተያያዘ የኩላሊት መድከም፣ በሕክምና ሲረዱ በቆዩበት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ዐርፈዋል፡፡

በሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ፣ ጥር 13 ቀን 1971 ዓ.ም. ለጅማ ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስነት የተሾሙት ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፡-

• ከ1971 እስከ 1976 ዓ.ም. የጅማ፣
• ከ1976 እስከ 1978 ዓ.ም. የካፋ፣
• ከ1978 እስከ 1981 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣
• ከ1981 እስከ 2001 ዓ.ም. የደቡብ ጎንደር፣
• ከ2001 እስከ 2011 ዓ.ም. የሰሜን ጎንደር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመኾን፣ ቤተ ክርስቲያንን ለ41 ዓመታት በትጋት አገልግለዋል፡፡

ጥንቱንም ለሢመተ ጵጵስና ለመመረጥ ያበቃቸው፣ ከማሕሌት ቁመት እስከ ዐውደ ምሕረት ስብከት የዘለቀው ሙሉ አገልግሎታቸው ሲኾን፣ በሕመም ምክንያት እስከተወሰኑበት ጊዜ ድረስ፣ ከተማና ገጠር ሳይመርጡ በትጋት፣ በደግነትና በሰላማዊነት አባታዊ ሓላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡

በፊት ስማቸው መሪጌታ አባ ኅሩይ ይባሉ የነበሩት ብፁዕነታቸው፣ በደብረ ጽጌ ገዳም ለዐሥራ አምስት ዓመታት አገልግለዋል፤ ለሢመት ተጠርተው ሲመረጡ፣ በጋሞጎፋ ሀገረ ስብከት በአገልግሎት ላይ ነበሩ፡፡ መጻሕፍተ ሐዲሳትንና ፍትሐ ነገሥትን፣ ከታዋቂው የነታ ገብረ ሕይወት ሐዲስ ተምረዋል፤ የቅኔና የአቋቋም ዐዋቂም ነበሩ፡፡

በአራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ እና በስድስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ምርጫ ወቅት፣ በዕጩነት ከቀረቡት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትም አንዱ ነበሩ፡፡

በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት፣ አፈር ውኃ እናት ወረዳ፣ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ገላውዴዎስ ደብር፣ በ1927 ዓ.ም. የተወለዱት የአንጋፋው አባት ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ሥርዐተ ቀብር፣ በኑዛዜያቸው መሠረት በዚያው ቤተ ክርስቲያን እንደሚፈጸም ታውቋል፡፡

በመጪው ሰኞ፣ በጎንደር መስቀል ዐደባባይ የስንብት መርሐ ግብር መዘጋጀቱ ተጠቁሟል፤ የሥርዐተ ቀብራቸውን ዕለትና ሰዓት፣ የርክበ ካህናት ምልአተ ጉባኤ ስብሰባውን በማካሔድ ላይ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኖ እንደሚያስታውቅ ይጠበቃል፡፡

የብፀዕነታቸው በረከት ይድረሰን፤ አሜን፡፡

Grateful ❣❣❣👏👏👑

youtube.com

Ethiopia: ሙሰኛ አባቶች እየተስተዋለ ለመጣው የሞራል ዝቅጠት ተጠያቂ ናቸው | Ethiopian | Abiy Ahmed

ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ
ወይ ፈጣሪ አምላክ እንደቸርነቱ ይመልከተን አባታችን ያሉት ትክክል ነዎት. የናንተ ፀሎት ይድረሥልን እንጅ እኛሥ ከትንሽ እሥከ ትልቅ በሀጥያት በዘረኝነት በጥላቻ ተመርዘናል ያለፉት አባቶች ፀሎት ይድረሥልን ግዜው በጣም ያሥፈራል ሠውም በፀሎት አልተጋነም.
My message to all EOTC religious fathers: “Keep your mouth free of perversity; keep corrupt talk far from your lips”. Proverbs 4:24. በእውነት መምህሮቻችን, አባቶችቻችን, በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እየደረሰባት ያለውን ጥፋት ካላዩ ካልሰሙ “መንጋውን ከተኩላ መጠበቅ ያልቻሉ ፣ የተኙ ወይም ቸልተኛ እረኛ ስለሆኑ የቅጽበት ቸልተኛነት የማያስፈልገውን ከፍተኛውን የስልጣነ ክህነት ማእረግ እባክዎትን ለትጉህ እረኞች ያስረክቡ”.
“Anyone who teaches something different is arrogant and lacks understanding. Such a person has an unhealthy desire to quibble over the meaning of words. This stirs up arguments ending in jealousy, division, slander, and evil suspicions. These people always cause trouble. Their minds are corrupt, and they have turned their backs on the truth. To them, a show of godliness is just a way to become wealthy”. 1 Timothy 6:4-5

“Now I urge you, brothers, to watch out for those who cause dissensions and obstacles contrary to the doctrine you have learned. Avoid them, for such people do not serve our Lord Christ but their own appetites. They deceive the hearts of the unsuspecting with smooth talk and flattering words”. Romans 16:17-18

https://www.youtube.com/watch?v=ZlSCA8CWUvg

youtube.com Browse EthioTimes to watch anything about #Ethiopia and #EthiopianNews https://goo.gl/MTZXJ8 . Ethiopia: ሙሰኛ አባቶች እየተስተዋለ ለመጣው የሞራል ዝቅጠት ተጠያቂ ናቸው | Ethiopian...

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Brisbane?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Videos (show all)

Location

Address


15 Eric Cres
Brisbane, QLD
4103
Other Religious Centers in Brisbane (show all)
Nexus Youth Brisbane Nexus Youth Brisbane
151 Flockton Street, Everton Park
Brisbane, 4053

Nexus Youth is the youth ministry of Nexus Church. Come and hang! Fridays 6:30-9pm at Nexus Church, 151 Flockton St Everton Park, Brisbane.

Theosophical Society Building, Brisbane Theosophical Society Building, Brisbane
355 Wickham Tce
Brisbane, 4000

Life&Legacy Church Brisbane Life&Legacy Church Brisbane
98 Anzac Avenue, Hillcrest
Brisbane, 4118

We’re a fresh ACC church in Logan, planted in 2016. We’re passionate about people encountering Jesus, being empowered, and experiencing authentic community in a vibrant church filled with music, food, fun, and life.

Grovely Christian Community Church Grovely Christian Community Church
38 Woking Street, Mitchelton
Brisbane, 4054

www.grovelychurch.org.au 38 Woking St, Mitchelton We are a group of Christians who meet together regularly to worship God and share His love with others.

Prince of Peace Lutheran College Prince of Peace Lutheran College
25 Henderson Rd
Brisbane, 4053

Ablaze Brisbane Ablaze Brisbane
204 Sherbrooke Road
Brisbane, 4110

Join us every FRIDAYS, 6:45-8:45 pm for a great time of worship, fellowship and learning the Word of God! Let's set our hearts ABLAZE!

Eastern Hills Anglicans Eastern Hills Anglicans
101 Watson St, Camp Hill
Brisbane, 4170

Eastern Hills AnglicansServing the eastern suburbs of Brisbane south of the river,we offers a relaxed, family oriented, modern style of service.

St George Greek Orthodox Church, Brisbane St George Greek Orthodox Church, Brisbane
33 Edmondstone St
Brisbane, 4101

The Greek Orthodox Church of St George, South Brisbane is a Parish-Community of the Greek Orthodox Archdiocese of Australia. It is the oldest and largest Greek Orthodox Church in Queensland.

The Pentecostals of Brisbane The Pentecostals of Brisbane
Daymar Street, Burbank
Brisbane, 4156

We are a multi-cultural church that cares about you. Our aim is to reflect the love of God so that you will feel loved and at home in our church family.

Gateway Church Gateway Church
1374 Old Cleveland Road, Carindale
Brisbane, 4152

We are a friendly, vibrant and exciting church full of vision and faith. We are a fun filled community with lots of passion and life having a real zeal for God. Our services are for the whole family.

Iglesia Beth-El Brisbane Iglesia Beth-El Brisbane
459 Annerley Road, Annerley
Brisbane, 4103

Iglesia Cristiana

Odin Norse gods Testament Odin Norse gods Testament
39 Harbour Rd
Brisbane, 4007

We are a group, looking at the correct historical details, religious perspective from Odin speech and the Norse goods. Meaning of the magic runes